በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የአብሮነት ዝግጅተን የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በጽ/ቤቱ በደመቀ መልኩ አካሂዷል።በዝግጅቱ ላይ የክፍለከተማችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጂናን ጨምሮ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በዕለቱም የክፍለከተማችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጂና አብሮነትን ማጠናከር ያለውን ፋይዳ ያነሱ ሲሆን በተለይ በመደጋገፍና በመረዳዳት ዙሪያ ያለንን እሴት ማጠናከር እንደሚግባ አውስተዋል በመጨረሻም ለእምነቱ ተከታዮች መልካም የገና በዓል ተመኝተዋል። በመድረኩ የህይወት ልምዳቸውን ያካፈሉት የብልፅግና ፓርቲ የክፍለከተማችን ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ለገሰ አስተማሪና አነቃቂ ተሞክሯቸውን ለተሳታፊዎች አካፍለዋል። በዝግጅቱም የክፍለከተማው የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ባልደረቦች የሚደግፏቸው አራት ልጆች የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ በወ/ሮ ውቢት ዮሃንስ ተበርክቶላቸዋል። በመጨረሻም በጽ/ቤቱ ኃላፊ በወ/ሮ ውቢት ዮሃንስ በተላለፈ መልክት አብሮነታችንን በማጠናከር ለውጤታማነታችን ማስቀጠያ መንገድ ስለሆነ በርትተን በመስራት የለመድነውን ውጤትና የስራ ስኬት መስመዝገብ ይገባናል ብለዋል።