የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ በመንግስት ድጋፍ ወደ ስራ ለማስገባት ለተከታታይ 12 ቀናት የሚቆይ በአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ በህይወት ክህሎት ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል ። በመርሃ ግብሩ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ እና የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ም/ዲን ወ/ሮ ፈንታዬ ባብሎ በቦታው በመገኘት የስልጠናውን ሂደት ተመልክተዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ እና የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የወጣቶችን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከሚያደርጉ አንዱ መሆኑን ጠቁመው የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የወጣቶች ስልጠና ወጭያቸው በመንግስት ተሸፍኖ ከድርጅቶቹ ጋር በማስተሳሰር ለስድስት ወር ያለማቋረጥ ከሰለጠኑ የሙያ ባለቤትነት ማረጋገጫ ሴርተፍኬት ከመግኘታቸው በላይ በስራ መስክ አማራጭ ስራ ዕድል የሚመቻች መሆኑን ገልጸዋል።