ከየወረዳው የብድር ፍላጎት ያላቸውን ኢንተርፕራይ......

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት

ከየወረዳው የብድር ፍላጎት ያላቸውን ኢንተርፕራይዞችንና ብድር ለመውስድ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ የሚመክር መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሂዷል። ህዳር 8 አቃቂ ቃሊቲ

ጥር 3-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

በዛሬው ዕለት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ብድር ፈላጊ ኢንተርፕራይዞችን ከብድር አቅራቢ የፋይናንስ ተቋማትና ባንኮች ጋር የሚመክር መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ከሁሉም ወረዳዎች የብድር ፍላጎት ያላቸው ኢንተርፕራይዞችና የብድር ሂደቱን ጀምረው ችግር ያገጠማቸው ማህበራት የተገኙ ሲሆን ከፋይናስና ከባንክ ዘርፉ ስኬት ባንክ፣አሀዱ ባንክ፣ቪዥን ፈንድ፣ ኦሮሚያ ህ/ስራ ባንክ፣አዲስ ካፒታልና ኬሪ ኢትዮጵያ የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ታደመዋል። በመድረኩም የተሳተፉ የፋይናንስ ተቋማትና ባንኮች ከራሳቸው አሰራር መነሻ በማድረግ ለኢንተርፕራይዞች ግንዘቤ አስጨብጠዋል። በተጨማሪም መድረኩ ኢንተርፕራይዞችም አማራጭ እንዲወስዱ እድልና ግንዛቤ የፈጠረ ሲሆን በስፋትም ብድር ለመውሰድ የበለጠ ፍላጎት አሳድሮባቸዋል፡፡ ኢንተርፕራይዞች በበኩላቸው የክ/ከተማ ስራ እና ክህሎት ፅ/ቤት መድረክ አዘጋጅቶ ግንዛቤ እንዲሰጥ ማድረጉን አመስግነው በቀጣይ በሂሳብ እና ንብረት አስተዳደር ስልጠና እንዲዘጋጅ ያላቸውን ፍላጎት አንስተዋል። ሌላው በመድረኩ ያነሱት አንዳንድ የፋይናንስ ተቋማት የብድር መስፈርትና የብድር የማግኝት ሂደት እጅግ ውስብስብና አሰልቺ መሆኑን ጠቅሰው ይህም እንዲስተካከልና ዛሬ በተፈጠረው ግልፀኝነትና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለመስተናገድ እንደሚችሉ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል ። በመጨረሻም የጽ/ቤቱ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አታኸልቲ ፀጋዬ ዛሬ የነበረን መድረክ በቀጣይም በየጊዜው የሚደረግና አፈፃፀሙን የምንገመግም ሲሆን ከአሰራር ጋር የተነሱ ሃሳቦችን የፋይናንስ ተቋማቱና ባንኮች ወስደው ማስተካከል እንዳለባቸው ገልፅው ዛሬ በተፈጠረው የግንዛቤ መድረክ ኢንተርፕራይዞች ያገኛችሁትን ግልፀኝነት በመጠቀም ቀጣይ ብድር መውሰድ የምትችሉበትን መብትና ግዴት የተረዳችሁ ሰለሆነ ከዚህ በፊት የሚያጋጥሟችሁ ችግሮችን ለመቀረፍ የሚቻልበትን መንገድ ዛሬ አግኝታችኃል ብዬ አምናለሁ ያሉ ሲሆን በቀጣይ በዚህ ዘረፍ የተሻለ አፈፃፀም መስመዝገብ እንደሚቻል አንስተው መድረኩ በመግባባት ተጠናቋል።