የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በሰኞ አብሮነት የዕውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር አካሂደዋል። በመርሃ ግብሩ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የተጋበዙት ዶክተር ገረመው ተክሉ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ልዩ እረዳት በማይንድ ሴት ዙሪያ እጅግ አስዳሳችና አስተማሪ ገለፃ ለባለሙያዎች ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ የታደሙት የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ሃሳባቸውን በስልጠናው ዙሪያ አንሸራሽረዋል። ስልጠናው የቀረበበት መንገድ አሳታፊና በቀላሉ ልንረዳው በምንችለው ሁኔታ መቀረቡ አስደስቶናል ሲሉ የስልጠናው ተሳታፊዎች የተናገሩ ሲሆን የዕለቱን አስልጣኛ ከልብ አመስግነዋል።በመጨረሻም የጽ/ቤቱ ም/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ የዛሬው ወርቃማ ሰኞ ከዚህ በፊት ከነበሩት በተሻለ መልኩ በዘርፉ ኤክስፐርቶች ስልጠና ያገኘንበትና ለመደበኛ ተግባራችን ስንቅ የያዝንበት ዕለት ነው ያሉ ሲሆን ። በቀጣይም የተለያዩ ባለሙያዎችን እየጋበዝን የዕውቀት ሽግግር ማድረጋችንን እንቀጥላለን ብለዋል። በመጨረሽም የወርቃማ ሰኞ መርሀግብር ሳይቆራረጥ ውጤታማ ሆኖ በመቀጠሉ የሶሻል ኮሚቴ አባላትንና ባለሙያዎችን አመስግነዋል።