"በአንድ ጀምበር ለ2 ሺህ ስራ ፈላጊዎች ስራ እ......

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት

"በአንድ ጀምበር ለ2 ሺህ ስራ ፈላጊዎች ስራ እድል መፈጠሩ ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጎልበት ባለፈ የተቋማት ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር የማይተካ ሚና አለዉ።" ፦ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ህዳር 02/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ

ጥር 3-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

"ስራ ዕድል ፈጠራ ከዳቦ በላይ ነው!" በሚል መሪ ሀሳብ በክ/ከተማው የስራ ክህሎት ጽ/ቤት አስተባባሪነት በአንድ ጀምበር ለ2000 ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ፈጠራ ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር ትስስር ተፈጠረ። በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ተመዝግበው የህይወት ክህሎት እና ሙያዊ ስልጠናዎችን ወስደዉ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ወጣቶችና ሴቶችን በአንድ ጀንበር ብቻ 2 ሺ ለሚሆኑት በ28 ቀጣሪ ድርጅቶች የስራ ዕድል እንደ ተፈጠረላቸው የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ገለፀዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ስራ እድል ፈጠራ የሀገር ኢኮኖሚን ማጠናከሪያ አንዱ መንገድ መሆኑን በመጥቀስ ስራ እድል የተፈጠረላቸዉ ወጣቶች በተፈጠረላቸዉ እደል ተጠቅመዉ እራሳቸዉን እና ሀገርን መለወጥ ላይ ትኩረት አድርገዉ መስራት እንዳለባቸዉ መልዕክት አስተላልፈዋል። አክለዉም ተቋማት የሰለጠነ የሰዉ ኃላይ ከጽ/ቤቱ ተረክቦ ወደ ተግባራ ለማስገባት ያሳዩት ቁርጠኝነት ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጎልበት ባለፈ ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር የማይተካ ሚና እንዳለዉ ገልፀዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሃንስ በበኩላቸው በክ/ከተማው ከ21ሺ በላይ ስራ አጥ ነዋሪዎችን የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰልጥነው እንደሚገኙ ገልፀው፤ በዛሬው ዕለት በአንድ ጀምበር ከ2ሺ በላይ ወጣቶችና ሴቶች በተለያየ ዘርፍ የስራ ዕድል ተፈጥሮ ትስስር እንደተፈጠረ፤ በየወሩ በተከታታይነት መሰል በአንድ ጀምበር ለበርካታ የስራ አጥ የስራ ዕድል እንደሚፈጠር እና በዋናነት የስራ አጡ ከስራ ማማረጥ ወጥቶ ባለዉ ፀጋ ወደ ስራ በመሰማራት ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ መልዕክት አስተለልፈዋል፡፡