የምርታማነት እምርታ ለዘላቂ ከፍታ!" በሚል መሪ......

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት

የምርታማነት እምርታ ለዘላቂ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚቀርቡበት ደማቅ ባዛር ተከፈተ።

ጥር 3-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር መጪውን የገና በዓል አስመልክቶ የአቅርቦት ችግር እንዳያጋጥም "የምርታማነት እምርታ ለዘላቁ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች የሚቀርቡበት ባዛር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዣንጥራር አባይ እና የክ/ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በተገኙበት ተጀምሯል። በማስጀመርያ መርሃግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዣንጥራር አባይ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት መሰል የግብይት አማራጮችን በመፍጠር የኑሮ ዉድነት እንዳይከሰት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን በመጥቀስ ማህበረሰቡ በአቅራቢያዉ የተፈጠረዉን እድል ተጠቅሞ በመገበያየት በቂ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በባዛሩ በርካታ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋትና በጥራት የቀረቡ መሆኑንና ባዛሩ የበዓል ገበያን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ በመግለፅ የክ/ከተማው ማህበረሰብ በባዛሮቹ በመገኘት የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበያይ ጥሪ አቅርበዋል። በባዛሩ የህብረት ስራ ሸማች ማህበራት፣ አምራች አርሶ አደሮች፣ ኢንተርፕራይዞች፣ ኢንዱስትሪዎች ወዘተ የተለያዩ ምርቶችን በቀጥታ ከአምራች ለሸማች እያቀረቡ እንደሚገኝ ተገልጿል።