የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ ዋስትና ዳሬክቶሬት የ10ሩን ክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች ፣ ባለሙያዎች ያሳተፈ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በስራና ክህሎት ጽ/ቤት አስተባባሪነት በተለያዩ ዘርፎች የተከናወነው ተግባራትን ተሞክሮ ለማስፋት ተዟዙረው ምልከታ አድርገዋል ። በጉብኝቱ ክ/ከተማ አስተዳደሩ በከተማችን አይነተኛ ለውጥ በማምጣት ላይ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ ምርት ቅርቦት ባዛሮችን ፣ የዶሮ እሴት ሰንሰለት ክላስተሮች በማስፋፋት በቂ ምርት ለተጠቃሚው በይዘትና በጥራት እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ ዜጎችን ከተረጂነት በማላቀቅ የስራ እድል ፈጠራ ምንጭ ከመሆን ባሻገር ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ የዋጋ ንረትን በማረጋጋት እና ምርት አቅርቦትን ከፍ እያደረጉ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑን ቡድኑ ገልጿል ።