ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና በመስጠት ብቃት ያለው ዜ......

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት

ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና በመስጠት ብቃት ያለው ዜጋ መፍጠር የጋራ ኃላፊነታችን ልንወጣ ይገባል ተባለ ። ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ

ጥር 3-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በስራና ክህሎት ጽ/ቤት ከአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም እና የቀጣይ 90 ቀናት ተግባራትን ገምግሟል ። የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስ እንደገለጹት በሁለቱም ዘርፎች ባለፉት በ6 ወራት ውስጥ በርካታ ዉጤታማ ተግባራት ማከናወን መቻሉን እና በቀሪ 90 ቀናት ስራ አጥ ወጣቶችን በመለየት ውጤታማ ለመሆንና በተጨባጭ ስራና እድል ለመፍጠር ክህሎት መር የሆነ ስልጠና በመስጠት ይበልጥ አጠናክሮ በመቀጠል ወጣቶች እና ሴቶች በስፋት በተለዩ ፀጋዎች አሰልጥኖ በማሰማራት የስራ እድል ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር እራሳቸውን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመቀየር ለሌሎች አርዕያ እንዲሆኑ ተቋማት በቅንጅት መስራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ከአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ዋና ዲን አቶ ፀጋየ አዱኛ የስልጠናውን ጥራት ማስጠበቅ ብቁና ብቃት ያለው ዜጋ ለመፍጠር ተግተን መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል ።