የሲቪክ ማህበራት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማና ቀ......

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት

የሲቪክ ማህበራት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማና ቀጣይ የ90 ቀናት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ። ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ

ጥር 3-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ስራ ክህሎት ጽ/ቤት የሲቪክ ማህበራት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማና ቀጣይ የ90 ቀናት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዷል። በውይይቱ የክ/ከተማው ምክትል ዋና አሰፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሃንስ፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ል ኃላፊ እና የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ጎሳ፣ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ ዘርጋ፤ ከ12ቱም ወረዳዎች የተውጣጡ የወጣቶችና ሴቶች ማህበራትና አደረጃጀቶች ተገኝተዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና አሰፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሃንስ በስራ አጥ ምዝገባና ወደ ስራ ማስገባት ስራዎች ለማሳካት በትኩረት መመራት እንደሚገባ ገልፀው፣ ወደ ሲስተም ያልገባ ስራ አጥ መረጃ ተገቢ ባለመሆኑ በመናበብ ሁኔታ በመስራት ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ በማመልከት በቀጣይ የአንድ ጀንበር የስራ ዕድል ፈጠራ በተባበረ ክንድ ማሳካት እንደሚገባ ተልዕኮ ሰጥተዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ል ኃላፊ እና የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ጎሳ በበኩላቸው የወጣቱን የስራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ መሳካት በቅንጅት፣ በተናበበ እንዲሁም ለአሰራር ስርዓት ተገዢ መሆን እንደሚገባው ጠቁመው፣ የወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት፣ የአካባቢ ሰላም ፀጥታ፣ ልማት ስራዎች ማዕከል ማድረግ እንደሚጠበቅ፣ ተግባራት እየገመገሙ ክፍተትን እየሞሉ መሄድ እንደሚገባ ገልጸዋል ። አክለውም በወጣቱ ሰርቶ መለወጥ አመለካከት ዙሪያ በትኩረት በመስራት በስራ ዕድል ተጠቃሚነት ግብር-ሀይል በማደራጀት ጭምር በማሳካት እንደሚገባ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡