በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት......

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ሰዉ ተኮር ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ጥር 3-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

ከነዚህም መካከል የወጣቶችና የሴቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ነዋሪዎችን ከስራ አጥነት ለማረጋገጥ በዛሬዉ እለት በአተማ ደረጃ ለ30 ሺህ ዜጎች ከተፈጠረዉ የስራ እድል መካከል የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር የስራ እድሉ ተጠቃሚዎችን በአስተዳደሩ ከተገነባዉ የG+4 መስሪያ ቦታ ህንፃ እና በወረዳ 7 የሚገኝ የእንስሳት ማደለቢያ ሼድ የክ/ከተማዉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለገሰ እና የክ/ከተማዉ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዉቢት ዮሐንስ በተገኙበት የእጣ ማዉጣት ስነ ስርአት ተካሄደ። በቀጣይም መሰል ዜጎችን ከስራ አጥነት የማላቀቅ ስራዎች በየዘርፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ተገልጿል። ህዳር 24/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ