በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት......

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የሳምንቱ የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በተለያዩ ዝግጅቶች በጽ/ቤቱ ተካሂዷል።

ጥር 3-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

ህዳር 22/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ የሰኞ አብሮነት የዕውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር በተለያዩ ዝግጅቶች ቀርበውበታል።በመርሃ ግብሩ ተግባራትን በዕውቀት መስራት እንዲቻል በየጊዜው የሚወርዱ አስራሮች ላይ ተላማዶ መፈፀምና ማስፈፀም የሚቻልበት ሁኔታ እንዲፈጠር ከተመረጡ ቡድኖች የአሰራር መመሪያዎች በስልጠና መልክ ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። በመቀጠል በመድረኩ የአንድ ጀንበር የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባርን በተመለከተ በጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሃንስ ገለፃ የቀረበ ሲሆን በተለይ የወረዳ ደጋፊዎች ተግባሩን ለማሳካት በልዩ ሁኔታ በጥብቅ እንዲሰሩ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። በተጨማሪም ሌሎች የጸ/ቤቱ መደበኛ ተግባራትም በትኩረትና በውጤታማነት እንዲመሩ መግባባት ላይ ተደርሱ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።