የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት እስከ ህዳር 30 ድረስ መጠናቀቅ ያለበት የ አንድ ጀምበር እና መደበኛ የስራ ዕድል ፈጠራ አፈፃፀም ከወረዳ ከምክትልና ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፣ ተወክለው ከነበሩ አመራሮች እንዲሁም ከስራ አስተባባሪዎች ጋር ገምግሟል ። በመርሃ ግብሩ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ በከተማ ግብርና ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፣ በቋሚና በግዚያዊ ስራ እድል ፈጠራ ፣ በብድር ስርጭትና አጠቃላይ አፈፃፀም የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል ። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሃንስ የአንድ ጀንበር የስራ እድል ፈጠራ የወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበትና ገቢን ማሳደግ የሚቻልበት በመሆኑ በቀሪ ቀናት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል። በተጨማሪም ስራ አጥ ወጣቶችና ሴቶች አምራች ዜጋ ሆነው እራሳቸውንና ማህበረሰቡን እንዲሁም ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገቱ ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ በቀረበላቸው የስራ እድል ፈጠራ ተሳታፊ እንዲሆኑ ሁላችንም የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።